ዘፍጥረት 28:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት።+ 19 ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል* አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ+ ነበር። ኢያሱ 16:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ለዮሴፍ ዘሮች+ በዕጣ የተሰጣቸው ምድር+ በኢያሪኮ አጠገብ ካለው ከዮርዳኖስ አንስቶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ውኃዎች ድረስ ሲሆን ከኢያሪኮ ሽቅብ የሚወጣውን ምድረ በዳ አቋርጦ እስከ ተራራማው የቤቴል አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።+ 1 ነገሥት 12:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው።
18 በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት።+ 19 ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል* አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ+ ነበር።
16 ለዮሴፍ ዘሮች+ በዕጣ የተሰጣቸው ምድር+ በኢያሪኮ አጠገብ ካለው ከዮርዳኖስ አንስቶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ውኃዎች ድረስ ሲሆን ከኢያሪኮ ሽቅብ የሚወጣውን ምድረ በዳ አቋርጦ እስከ ተራራማው የቤቴል አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።+
28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው።