1 ነገሥት 12:31, 32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እሱም በኮረብቶቹ ላይ የአምልኮ ቤቶችን ሠራ፤ ከሕዝቡም መካከል ሌዋውያን ያልሆኑ ሰዎችን ካህናት አድርጎ ሾመ።+ 32 በተጨማሪም ኢዮርብዓም በስምንተኛው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን በይሁዳ ይከበር የነበረው ዓይነት በዓል እንዲቋቋም አደረገ።+ ለሠራቸውም ጥጆች በቤቴል+ በሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ በቤቴል ለሠራቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችም ካህናት መደበ። 1 ነገሥት 13:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+
31 እሱም በኮረብቶቹ ላይ የአምልኮ ቤቶችን ሠራ፤ ከሕዝቡም መካከል ሌዋውያን ያልሆኑ ሰዎችን ካህናት አድርጎ ሾመ።+ 32 በተጨማሪም ኢዮርብዓም በስምንተኛው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን በይሁዳ ይከበር የነበረው ዓይነት በዓል እንዲቋቋም አደረገ።+ ለሠራቸውም ጥጆች በቤቴል+ በሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ በቤቴል ለሠራቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችም ካህናት መደበ።
33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+