33 ለቤተ መቅደሱ መግቢያ የሚሆኑትንና የአንድ አራተኛው ክፍል የሆኑትን የጥድ እንጨት መቃኖች የሠራው በዚሁ መንገድ ነበር። 34 እሱም ከጥድ እንጨት ሁለት በሮች ሠራ። ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት አንዱ በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ፣ ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት ሌላኛውም በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ ተገጥሞ ነበር።+ 35 እሱም ኪሩቦችን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸ፤ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።