-
ዘፍጥረት 19:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። እሱም ባያቸው ጊዜ ተነስቶ ወደ እነሱ ሄደ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።+ 2 እንዲህም አለ፦ “ጌቶቼ፣ እባካችሁ ወደ አገልጋያችሁ ቤት ጎራ በሉና እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ። ከዚያም በማለዳ ተነስታችሁ ጉዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” እነሱም መልሰው “አይሆንም፣ አደባባዩ ላይ እናድራለን” አሉ። 3 እሱ ግን አጥብቆ ስለለመናቸው አብረውት ወደ ቤቱ ሄዱ። ከዚያም ግብዣ አደረገላቸው። ቂጣም ጋገረላቸው፤ እነሱም በሉ።
-
-
መሳፍንት 13:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ማኑሄም የይሖዋን መልአክ “እባክህ አንድ የፍየል ጠቦት አዘጋጅተን እስክናቀርብልህ ድረስ ቆይ” አለው።+
-