-
1 ነገሥት 8:63, 64አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
63 ሰለሞን 22,000 ከብቶችና 120,000 በጎች ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት+ አድርጎ አቀረበ። በዚህ መንገድ ንጉሡና እስራኤላውያን በሙሉ የይሖዋን ቤት መረቁ።+ 64 ንጉሡም በዚያ ቀን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል መቀደስ አስፈልጎት ነበር፤ ምክንያቱም የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን በዚያ ማቅረብ ነበረበት፤ ይህም የሆነው በይሖዋ ፊት ያለው የመዳብ መሠዊያ+ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ስብ+ መያዝ ስላልቻለ ነው።
-