-
1 ነገሥት 1:38-40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ከዚያም ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያህ፣+ ከሪታውያንና ጴሌታውያን+ ወርደው ሰለሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ አስቀመጡት፤+ ወደ ግዮንም+ አመጡት። 39 ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ+ ውስጥ የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ ሰለሞንን ቀባው፤+ እነሱም ቀንደ መለከት መንፋት ጀመሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” እያለ ይጮኽ ጀመር። 40 ከዚያም ሕዝቡ በሙሉ ዋሽንት እየነፋና በደስታ እየፈነደቀ ተከትሎት ወጣ፤ ከጩኸታቸውም የተነሳ ምድሪቱ ተሰነጠቀች።+
-