13 ለካህኑ ለአሮን ልጆችም ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን ኬብሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሊብናን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ 14 ያቲርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ኤሽተሞዓን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ 15 ሆሎንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ደቢርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ 16 አይንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዩጣን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቤትሼሜሽን ከነግጦሽ መሬቷ ሰጡ፤ ከእነዚህ ሁለት ነገዶች ላይ ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ።