-
ኢያሱ 21:34-40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 የሜራራውያን ቤተሰቦች+ የሆኑት የቀሩት ሌዋውያን ደግሞ ከዛብሎን ነገድ+ ላይ ዮቅነአምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ቃርታን ከነግጦሽ መሬቷ፣ 35 ዲምናን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ናሃላልን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ወሰዱ።
36 ከሮቤል ነገድ ላይ ቤጼርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ያሃጽን ከነግጦሽ መሬቷ፣+ 37 ቀደሞትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም መፋአትን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
38 ከጋድ ነገድ+ ላይ ደግሞ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ማሃናይምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ 39 ሃሽቦንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ያዜርን+ ከነግጦሽ መሬቷ በአጠቃላይ አራት ከተሞችን ሰጡ።
40 ከሌዋውያን ቤተሰቦች ለቀሩት ሜራራውያን በየቤተሰባቸው በዕጣ የተሰጧቸው ከተሞች በአጠቃላይ 12 ከተሞች ነበሩ።
-