ዘፀአት 33:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር እንደሚነጋገር ይሖዋ ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር።+ ሙሴ ወደ ሰፈሩ በሚመለስበት ጊዜ አገልጋዩና ረዳቱ+ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ከድንኳኑ አይለይም ነበር። ዘኁልቁ 11:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ ጊዜ ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፣ እነዚህን ሰዎች ከልክላቸው እንጂ!”+ ሲል ተናገረ። ዘኁልቁ 32:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ‘ከግብፅ ምድር ከወጡት መካከል 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማልኩላቸውን+ ምድር አያዩም፤+ ምክንያቱም በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ 12 ይሖዋን በሙሉ ልባቸው ከተከተሉት+ ከቀኒዛዊው ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና+ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ በስተቀር አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም።’ ዘዳግም 34:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+ ኢያሱ 1:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 1 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ ይሖዋ የሙሴ አገልጋይ+ የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን*+ እንዲህ አለው፦
11 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር እንደሚነጋገር ይሖዋ ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር።+ ሙሴ ወደ ሰፈሩ በሚመለስበት ጊዜ አገልጋዩና ረዳቱ+ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
11 ‘ከግብፅ ምድር ከወጡት መካከል 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማልኩላቸውን+ ምድር አያዩም፤+ ምክንያቱም በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ 12 ይሖዋን በሙሉ ልባቸው ከተከተሉት+ ከቀኒዛዊው ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና+ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ በስተቀር አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም።’
9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+