12 ነዶው ወዲያና ወዲህ እንዲወዘወዝ በምታደርጉበት ቀን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው እንከን የሌለበት ጠቦት ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ማቅረብ አለባችሁ። 13 ከዚህም ጋር ሁለት አሥረኛ ኢፍ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። በተጨማሪም አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከዚያ ጋር የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።