-
መሳፍንት 14:5, 6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም።
-
-
2 ሳሙኤል 23:20-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው* ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ 21 በተጨማሪም እጅግ ግዙፍ የሆነ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ የነበረ ቢሆንም እሱ ግን በትር ብቻ ይዞ በመሄድ ገጠመው፤ የግብፃዊውንም ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው። 22 የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። 23 ከሠላሳዎቹ ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው።
-