-
2 ሳሙኤል 6:3-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በኮረብታ ላይ ካለው ከአቢናዳብ+ ቤት ለማምጣት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤+ የአቢናዳብ ልጆች የሆኑት ዖዛ እና አሂዮም አዲሱን ሠረገላ ይነዱ ነበር።
4 በመሆኑም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በኮረብታ ላይ ከነበረው ከአቢናዳብ ቤት ይዘው ጉዞ ጀመሩ፤ አሂዮም ከታቦቱ ፊት ፊት ይሄድ ነበር። 5 ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት ከጥድ እንጨት በተሠሩ የተለያዩ መሣሪያዎች፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣+ በአታሞ፣+ በጸናጽልና በሲምባል*+ ታጅበው በይሖዋ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። 6 ወደ ናኮን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ያዘ።+ 7 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ዖዛ እንዲህ ያለ የድፍረት ድርጊት+ በመፈጸሙ እውነተኛው አምላክ እዚያው ቀሰፈው፤+ እሱም በእውነተኛው አምላክ ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ። 8 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤* ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ* ተብሎ ይጠራል።
-