31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ 32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+ 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር አብረው የሚያገለግሉት ሰዎች እነዚህ ነበሩ፦ ከቀአታውያን መካከል ዘማሪው ሄማን፣+ የኢዩኤል+ ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣