-
1 ዜና መዋዕል 16:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ያከብሩ፣* ያመሰግኑና ያወድሱ ዘንድ የተወሰኑ ሌዋውያንን በይሖዋ ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ ሾመ።+ 5 መሪው አሳፍ+ ነበር፤ ከእሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ የኢዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ማቲትያህ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል+ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይጫወቱ ነበር፤+ አሳፍ ደግሞ ሲምባል ይጫወት ነበር፤+ 6 ካህናቱ በናያህ እና ያሃዚኤል በእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ዘወትር መለከት ይነፉ ነበር።
-