-
1 ሳሙኤል 17:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ዳዊት ሳኦልን ያገለግል እንዲሁም ከዚያ እየተመላለሰ በቤተልሔም የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር።+
-
-
1 ሳሙኤል 25:30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ይሖዋ ቃል የገባለትን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በሚፈጽምለትና በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሚሾመው+ ጊዜ
-
-
2 ሳሙኤል 7:8-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ። 9 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።+ 10 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎች እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤+ 11 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። እኔም ከጠላቶችህ ሁሉ እረፍት እሰጥሃለሁ።+
-