-
2 ሳሙኤል 7:21-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ለቃልህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ* እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል፤ እንዲሁም ለአገልጋይህ ገልጠህለታል።+ 22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእርግጥም ታላቅ+ የሆንከው ለዚህ ነው። እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። 23 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ አምላክ ሄዶ ለእነሱ ሲል ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን+ በመፈጸም እንዲሁም ስሙን በማስጠራት+ ሕዝቡ አድርጎ ዋጃቸው።+ ከግብፅ ለዋጀኸው ሕዝብ ስትል ብሔራትንና አማልክታቸውን አባረርክ። 24 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጸናኸው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+
-