15 ከዚያም ይሖዋ ከጠዋት አንስቶ እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤+ በዚህም የተነሳ ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ ካለው ሕዝብ መካከል 70,000 ሰዎች ሞቱ።+ 16 መልአኩም ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን ወደ እሷ በዘረጋ ጊዜ ይሖዋ በደረሰው ጥፋት ተጸጸተ፤+ በመሆኑም በሕዝቡ ላይ ጥፋት እያመጣ የነበረውን መልአክ “ይብቃ! አሁን እጅህን መልስ” አለው። የይሖዋ መልአክ በኢያቡሳዊው+ በአረውና+ አውድማ አጠገብ ነበር።