-
ዘዳግም 4:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው።+ እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው።
-
-
2 ነገሥት 23:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 የይሁዳ ነገሥታት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ በነበሩት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ላይ የሚጨስ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ የሾሟቸውን የባዕድ አምላክ ካህናት አባረረ፤ በተጨማሪም ለባአል፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ዞዲያክ ለተባለው ኅብረ ከዋክብትና ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ+ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ የነበሩትን በሙሉ አባረረ።
-