-
1 ነገሥት 7:47አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
47 ሰለሞን ዕቃዎቹ ሁሉ እንዲመዘኑ አላደረገም፤ ምክንያቱም ዕቃዎቹ እጅግ ብዙ ነበሩ። የመዳቡ ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም።+
-
-
1 ዜና መዋዕል 22:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በተጨማሪም ዳዊት ለመግቢያዎቹ በሮች የሚያስፈልጉ ምስማሮችንና ማጠፊያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ከፍተኛ መጠን ያለው ብረት አዘጋጀ፤ ደግሞም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብ አከማቸ፤+
-
-
ኤርምያስ 52:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ ቤት ያሠራቸው ሁለቱ ዓምዶች፣ ባሕሩ፣ ከባሕሩ ሥር ያሉት 12 የመዳብ በሬዎችና+ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹ የተሠሩበት መዳብ ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የሚችል አልነበረም።
-