ዘፀአት 12:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።+ አዎ፣ በመጀመሪያው ቀን ከቤታችሁ እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ እርሾ የገባበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው* ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። ዘሌዋውያን 23:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል።+ ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል።+ ዘዳግም 16:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤+ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው።+ 2 ዜና መዋዕል 30:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ሕዝቅያስ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን*+ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት እንዲመጡ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሁሉ መልእክት ላከ፤+ ለኤፍሬምና ለምናሴም እንኳ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፈ።+ 2 ዜና መዋዕል 30:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 በመሆኑም በኢየሩሳሌም የተገኙት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል+ ለሰባት ቀናት በታላቅ ደስታ አከበሩ፤+ ሌዋውያኑና ካህናቱም ከፍ ባለ ድምፅ ለይሖዋ የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን በመጫወት በየዕለቱ ይሖዋን ያወድሱ ነበር።+
15 ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።+ አዎ፣ በመጀመሪያው ቀን ከቤታችሁ እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ እርሾ የገባበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው* ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።
3 ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤+ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው።+
30 ሕዝቅያስ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን*+ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት እንዲመጡ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሁሉ መልእክት ላከ፤+ ለኤፍሬምና ለምናሴም እንኳ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፈ።+
21 በመሆኑም በኢየሩሳሌም የተገኙት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል+ ለሰባት ቀናት በታላቅ ደስታ አከበሩ፤+ ሌዋውያኑና ካህናቱም ከፍ ባለ ድምፅ ለይሖዋ የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን በመጫወት በየዕለቱ ይሖዋን ያወድሱ ነበር።+