-
ሕዝቅኤል 17:12-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ።+ 13 በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ+ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው።+ ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤+ 14 ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው።+ 15 ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና+ ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ+ በእሱ ላይ ዓመፀ።+ ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’+
-