የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 28:11-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “‘በየወሩም* መባቻ ላይ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ 12 ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ 13 ለእያንዳንዱም ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። 14 በተጨማሪም ከእነዚህ ጋር ለአንድ ወይፈን ግማሽ ሂን፣+ ለአውራው በግ አንድ ሦስተኛ ሂን+ እንዲሁም ለአንድ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን+ የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። ይህም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚቀርብ ወርሃዊ የሚቃጠል መባ ነው። 15 እንዲሁም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ ሆኖ ለይሖዋ መቅረብ አለበት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ