10 የሳባ ንግሥት ስለ ሰለሞን ዝና እንዲሁም ከይሖዋ ስም ጋር ስላለው ግንኙነት ሰማች፤+ በመሆኑም አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው መጣች።+ 2 እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ+ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣+ በጣም ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ኢየሩሳሌም ደረሰች። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው። 3 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ንጉሡ ሊያብራራላት ያልቻለው ምንም ነገር አልነበረም።