-
1 ነገሥት 11:30, 31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 አኪያህም ለብሶት የነበረውን አዲስ ልብስ ይዞ 12 ቦታ ቀደደው። 31 ከዚያም ኢዮርብዓምን እንዲህ አለው፦
“አሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እንግዲህ መንግሥቱን ከሰለሞን እጅ እቀደዋለሁ፤ ለአንተም አሥር ነገዶችን እሰጥሃለሁ።+
-
-
1 ነገሥት 14:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 በመሆኑም ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ፣ ተነሺና የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን እንዳያውቁ ራስሽን ለውጠሽ ወደ ሴሎ ሂጂ። ነቢዩ አኪያህ ያለው እዚያ ነው። እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ንጉሥ እንደምሆን የተናገረው እሱ ነው።+
-
-
1 ነገሥት 14:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 አኪያህም በሩ ጋ ስትደርስ የእግሯን ኮቴ ሰምቶ እንዲህ አላት፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ግቢ። ማንነትሽ እንዳይታወቅ ራስሽን የለወጥሽው ለምንድን ነው? መጥፎ ዜና እንድነግርሽ ታዝዣለሁ።
-