-
1 ነገሥት 12:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በዚህ ጊዜ “እንግዲያው ሂዱና ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው። በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ።+ 6 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም አባቱ ሰለሞን በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሲያገለግሉት የነበሩትን ሽማግሌዎች “ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” በማለት ምክር ጠየቀ። 7 እነሱም “ዛሬ አንተ የዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆንና የጠየቁህን ብትፈጽምላቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ” በማለት መለሱለት።
-