-
1 ነገሥት 15:17-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ እሱም ማንም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ እንዳይገባና እንዳይወጣ* ለማድረግ ራማን+ መገንባት* ጀመረ።+ 18 በዚህ ጊዜ አሳ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ ሁሉ አውጥቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው። ከዚያም ንጉሥ አሳ እነዚህን አገልጋዮቹን በደማስቆ ወደሚገኘው የሶርያ ንጉሥ+ ማለትም የሄዝዮን ልጅ፣ የታብሪሞን ልጅ ወደሆነው ወደ ቤንሃዳድ እንዲህ ሲል ላካቸው፦ 19 “በእኔና በአንተ እንዲሁም በአባቴና በአባትህ መካከል ውል* አለ። እኔ የብርና የወርቅ ስጦታ ልኬልሃለሁ። ስለዚህ ና፣ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ እንዲርቅ ከእሱ ጋር የገባኸውን ውል* አፍርስ።”
-