-
1 ነገሥት 15:20-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ቤንሃዳድ የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ የጦር ሠራዊቱን አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እነሱም ኢዮንን፣+ ዳንን፣+ አቤልቤትማዓካን እንዲሁም ኪኔሬትን ሁሉና መላውን የንፍታሌም ምድር መቱ። 21 ባኦስም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ ራማን መገንባቱን* አቁሞ በቲርጻ+ መኖሩን ቀጠለ። 22 ከዚያም ንጉሥ አሳ ማንንም ሳያስቀር የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነሱም ባኦስ እየገነባባቸው የነበሩትን የራማን ድንጋዮችና ሳንቃዎች አጋዙ፤ ንጉሥ አሳም በድንጋዮቹና በሳንቃዎቹ በቢንያም የምትገኘውን ጌባንና+ ምጽጳን+ ገነባ።*
-