-
2 ዜና መዋዕል 26:11-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 በተጨማሪም ዖዝያ ለውጊያ ዝግጁ የሆነ ሠራዊት ነበረው። በቡድን በቡድን ተደራጅተው ለጦርነት ይወጡ ነበር። እነዚህ ሰዎች ከንጉሡ መኳንንት አንዱ በሆነው በሃናንያህ አመራር ሥር ሆነው በሚያገለግሉት በጸሐፊው የኢዔል+ እና በአለቃው ማአሴያህ አማካኝነት ተቆጥረው ተመዘገቡ።+ 12 በእነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች ላይ የተሾሙት የአባቶች ቤት መሪዎች አጠቃላይ ቁጥር 2,600 ነበር። 13 በእነሱ አመራር ሥር 307,500 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበር፤ ይህም ንጉሡ በጠላት ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ድጋፍ የሚሰጡ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን የያዘ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ነው።+
-