29 “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ+ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።+ 30 ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ስትገባና እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንተ ላይ ሲደርሱ ያኔ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ትመለሳለህ፤ ድምፁንም ትሰማለህ።+ 31 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው።+ አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።+