27 የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ+ ይህን ሲያይ በአትክልት ቤቱ በኩል ባለው መንገድ ሸሸ። (በኋላም ኢዩ እሱን እያሳደደው “እሱንም ግደሉት!” አለ። እነሱም በይብለአም+ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጉር ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ ላይ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቆሰሉት። እሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ። 28 ከዚያም አገልጋዮቹ በሠረገላ ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊት ከተማ+ ከአባቶቹ ጋር በራሱ መቃብር ቀበሩት።