19 በተጨማሪም ንጉሡን አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች እንዲያመጡት መቶ አለቆቹን፣+ ካራውያን ጠባቂዎቹን፣ የቤተ መንግሥት ዘቦቹንና+ የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ እነሱም ወደ ቤተ መንግሥቱ ዘቦች በር በሚወስደው መንገድ በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ። እሱም በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ተቀመጠ።+ 20 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በንጉሡ ቤት በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት።