-
ዘፀአት 30:12-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “የሕዝብ ቆጠራ በማካሄድ የእስራኤልን ልጆች በምትቆጥርበት+ ጊዜ ሁሉ እያንዳንዱ ሰው በቆጠራው ወቅት ለይሖዋ ስለ ሕይወቱ* ቤዛ መስጠት አለበት። ይህን የሚያደርጉት በሚመዘገቡበት ጊዜ መቅሰፍት እንዳይመጣባቸው ነው። 13 የተመዘገቡት ሁሉ የሚሰጡት ይህን ነው፦ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት+ ግማሽ ሰቅል* ይሰጣሉ። አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ* ነው። ለይሖዋ የሚሰጠው መዋጮ ግማሽ ሰቅል ነው።+ 14 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ሁሉ ለይሖዋ መዋጮ ይሰጣሉ።+ 15 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ እንዲሆን ለይሖዋ መዋጮ በምትሰጡበት ጊዜ ባለጸጋው ከግማሽ ሰቅል* አብልጦ፣ ችግረኛውም ከግማሽ ሰቅል አሳንሶ አይስጥ። 16 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ በመሆን በይሖዋ ፊት ለእስራኤላውያን እንደ መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስተሰረያ የቀረበውን የብር ገንዘብ ከእስራኤላውያን ወስደህ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት ትሰጠዋለህ።”
-