-
2 ነገሥት 14:1-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ ነገሠ። 2 አሜስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ የሆዓዲን የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ 3 እሱም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ባይሆንም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ፈጸመ።+ ሁሉንም ነገር አባቱ ኢዮዓስ እንዳደረገው አደረገ።+ 4 ሆኖም ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤+ ሕዝቡ አሁንም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ 5 እሱም መንግሥቱ በእጁ እንደጸናለት፣ ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን አገልጋዮቹን+ ገደላቸው። 6 ይሁንና “አባቶች በልጆቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም በአባቶቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ ሰው በገዛ ኃጢአቱ ይገደል”+ በሚለው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው የይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም።
-