-
2 ነገሥት 14:17-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ+ 15 ዓመት ኖረ።+ 18 የቀረው የአሜስያስ ታሪክ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? 19 ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ውስጥ በእሱ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ፤+ እሱም ወደ ለኪሶ ሸሸ፤ እነሱ ግን ተከታትለው እንዲይዙት ሰዎችን ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። 20 ከዚያም በፈረሶች ላይ ጭነው አመጡት፤ እሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር በኢየሩሳሌም ተቀበረ።+
-