10 በመሆኑም አሳ በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 11 በዚያም ቀን፣ ካመጡት ምርኮ ላይ 700 ከብቶችንና 7,000 በጎችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። 12 በተጨማሪም የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ለመፈለግ ቃል ኪዳን ገቡ።+ 13 የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የማይፈልግ ማንኛውም ሰው ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል ተስማሙ።+