1 ዜና መዋዕል 15:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከዚያም ዳዊት በሙዚቃ መሣሪያዎች ይኸውም በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገና+ እና በሲምባል+ ታጅበው በደስታ ይዘምሩ ዘንድ ዘማሪ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ አለቆች ነገራቸው። 17 በመሆኑም ሌዋውያኑ የኢዩኤልን ልጅ ሄማንን፣+ ከወንድሞቹም መካከል የቤራክያህን ልጅ አሳፍን፣+ እንዲሁም ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከሜራራውያን መካከል የቁሻያህን ልጅ ኤታንን+ ሾሙ። 1 ዜና መዋዕል 25:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ 2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች መካከል ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያህ እና አሼርዔላ፤ እነዚህ በአሳፍ አመራር ሥር ያሉ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ሲሆኑ በንጉሡ አመራር ሥር ሆነው ትንቢት ይናገሩ ነበር።
16 ከዚያም ዳዊት በሙዚቃ መሣሪያዎች ይኸውም በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገና+ እና በሲምባል+ ታጅበው በደስታ ይዘምሩ ዘንድ ዘማሪ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ አለቆች ነገራቸው። 17 በመሆኑም ሌዋውያኑ የኢዩኤልን ልጅ ሄማንን፣+ ከወንድሞቹም መካከል የቤራክያህን ልጅ አሳፍን፣+ እንዲሁም ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከሜራራውያን መካከል የቁሻያህን ልጅ ኤታንን+ ሾሙ።
25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ 2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች መካከል ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያህ እና አሼርዔላ፤ እነዚህ በአሳፍ አመራር ሥር ያሉ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ሲሆኑ በንጉሡ አመራር ሥር ሆነው ትንቢት ይናገሩ ነበር።