2 ሳሙኤል 5:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ፤ ስፍራውም የዳዊት ከተማ ተብሎ ይጠራ ነበር፤* እሱም ከጉብታው*+ አንስቶ ወደ ውስጥ ዙሪያውን መገንባት ጀመረ።+ 1 ነገሥት 9:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የፈርዖን ሴት ልጅ+ ግን ከዳዊት ከተማ+ ወጥታ ሰለሞን ወዳሠራላት ወደ ራሷ ቤት መጣች፤ ከዚያም ጉብታውን*+ ሠራ። 1 ነገሥት 11:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 በንጉሡ ላይ ያመፀውም በዚህ የተነሳ ነው፦ ሰለሞን ጉብታውን*+ ሠርቶ እንዲሁም በአባቱ በዳዊት ከተማ+ ቅጥር ላይ የነበረውን ክፍተት ዘግቶ ነበር። 2 ነገሥት 12:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ይሁንና አገልጋዮቹ በኢዮዓስ ላይ በማሴር+ ወደ ሲላ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ በጉብታው+ ቤት* ገደሉት።