-
1 ዜና መዋዕል 9:22-27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በደጆቹ ላይ ቆመው እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ 212 ነበሩ። እነሱም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት+ በሰፈሮቻቸው ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዳዊትና ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል እነዚህን ሰዎች ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ሾሟቸው። 23 እነሱና ወንዶች ልጆቻቸው የይሖዋን ቤት ይኸውም የማደሪያ ድንኳኑን* በሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 24 በር ጠባቂዎቹ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ በኩል ነበሩ።+ 25 በየሰፈሮቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻቸው ለሰባት ቀናት አብረዋቸው ለማገልገል አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር። 26 ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ የሚያገለግሉ አራት የበር ጠባቂ አለቆች* ነበሩ። እነሱም ሌዋውያን ሲሆኑ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙትን ክፍሎችና* ግምጃ ቤቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 27 በእውነተኛው አምላክ ቤት ዙሪያ በተመደቡበት ቦታ ላይ ሆነው ያድሩ ነበር፤ የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እንዲሁም ቁልፉ የተሰጣቸውና ቤቱን በየጠዋቱ የሚከፍቱት እነሱ ነበሩ።
-