5 ከዚያም ምሽት ላይ የእህል መባው+ በሚቀርብበት ጊዜ እጀ ጠባቤና መደረቢያዬ እንደተቀደደ ራሴን አዋርጄ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ፤ በጉልበቴም ተንበርክኬ እጆቼን ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ዘረጋሁ። 6 እንዲህም አልኩ፦ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፣ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ማድረግ አሳፈረኝ፤ አሸማቀቀኝ፤ ምክንያቱም አምላኬ ሆይ፣ የፈጸምናቸው ስህተቶች በአናታችን ላይ ተቆልለዋል፤ በደላችንም ከመብዛቱ የተነሳ እስከ ሰማይ ደርሷል።+