የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዕዝራ 9:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 እነዚህ ነገሮች እንደተጠናቀቁ መኳንንቱ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ይኸውም ከከነአናውያን፣ ከሂታውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብፃውያንና+ ከአሞራውያን+ እንዲሁም አስጸያፊ ከሆኑት ልማዶቻቸው+ ራሳቸውን አልለዩም። 2 ከእነሱም ሴቶች ልጆች መካከል ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስቶች ወስደዋል።+ በመሆኑም ቅዱስ ዘር+ የሆኑት እነዚህ ሰዎች በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ጋር ተቀላቅለዋል።+ ይህን ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በመፈጸም ግንባር ቀደም የሆኑት መኳንንቱና የበታች ገዢዎቹ ናቸው።”

  • ነህምያ 13:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ+ ልጅ ከዮያዳ+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዱ የሆሮናዊው የሳንባላጥ+ አማች ሆኖ ነበር። በመሆኑም ከአጠገቤ አባረርኩት።

  • ሕዝቅኤል 44:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 መበለት የሆነች ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት አያግቡ፤+ ይሁንና የእስራኤል ዘር የሆነች ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረች መበለት ማግባት ይችላሉ።’+

  • ሚልክያስ 2:7, 8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን* ከአፉ ሊሹ ይገባል፤+ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው።

      8 “እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል። ብዙዎች ከሕጉ ጋር በተያያዘ* እንዲሰናከሉ አድርጋችኋል።+ የሌዊን ቃል ኪዳን አርክሳችኋል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ