-
ነህምያ 7:61-65አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
61 ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦+ 62 የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 642። 63 ከካህናቱም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ+ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ+ ወንዶች ልጆች። 64 እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊገኙ አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ።*+ 65 ገዢውም*+ በኡሪምና በቱሚም+ አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይኖርባቸው ነገራቸው።+
-