33 በአንድ በኩል ይሖዋን ይፈሩ ነበር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመፈናቀላቸው በፊት የነበሩባቸው ብሔራት ያመልኩ እንደነበረው የራሳቸውን አማልክት ያመልኩ ነበር።+
34 እስከ ዛሬ ድረስ አምልኳቸውን የሚያከናውኑት በፊት ያደርጉት እንደነበረው ነው። ይሖዋን የሚያመልክ ብሎም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹን እንዲሁም ይሖዋ እስራኤል የሚል ስም ላወጣለት ለያዕቆብ+ ልጆች የሰጣቸውን ሕግና ትእዛዝ የሚከተል አንድም ሰው አልነበረም።