14 እኛ ደግሞ የቤተ መንግሥቱን ጨው እየበላን የንጉሡ ጥቅም ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ መስሎ አልታየንም፤ በመሆኑም ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ለማድረግ ይህን ደብዳቤ ልከናል፤ 15 ስለዚህ የቀድሞ አባቶችህ መዝገብ ይመርመር።+ ይህች ከተማ ዓመፀኛና ነገሥታትንም ሆነ አውራጃዎችን ጉዳት ላይ የምትጥል፣ ከጥንት ጀምሮም ዓመፅ ቆስቋሾችን ሸሽጋ የምታኖር መሆኗን ከእነዚህ መዛግብት መረዳት ትችላለህ። ከተማዋም የተደመሰሰችው በዚህ የተነሳ ነው።+