-
2 ዜና መዋዕል 26:18, 19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ከዚያም ንጉሥ ዖዝያን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ፣ አንተ ለይሖዋ ዕጣን ማጠንህ ተገቢ አይደለም!+ ዕጣን ማጠን ያለባቸው ካህናቱ ብቻ ናቸው፤ እነሱ የተቀደሱ የአሮን ዘሮች ናቸውና።+ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ስለፈጸምክ ከመቅደሱ ውጣ፤ እንዲህ ማድረግህ በይሖዋ አምላክ ዘንድ ምንም ዓይነት ክብር አያስገኝልህም።”
19 ዕጣን ለማጠን በእጁ ጥና ይዞ የነበረው ዖዝያ ግን እጅግ ተቆጣ፤+ ካህናቱን እየተቆጣ ሳለም በይሖዋ ቤት በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ካህናቱ ባሉበት ግንባሩ ላይ የሥጋ ደዌ+ ወጣበት።
-