የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 24:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+

  • 2 ነገሥት 24:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ከሰይፍ የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤+ እነሱም የፋርስ መንግሥት* መግዛት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ+ የእሱና የወንዶች ልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ፤+

  • ኤርምያስ 39:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ በከተማዋ ውስጥ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ከድተው ለእሱ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች እንዲሁም የቀሩትን ሁሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።

  • ኤርምያስ 52:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ችግረኛ ከሆኑት ሰዎች መካከል የተወሰኑትንና በከተማዋ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች አጋዘ። በተጨማሪም ከድተው ለባቢሎን ንጉሥ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎችና የቀሩትን የተካኑ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወሰደ።+

  • ኤርምያስ 52:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ናቡከደነጾር* በግዞት የወሰዳቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፦ በሰባተኛው ዓመት 3,023 አይሁዳውያንን ወሰደ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ