ዘዳግም 31:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና* በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ።+ 2 ዜና መዋዕል 17:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከእነሱ ጋር ሌዋውያኑ ሸማያህ፣ ነታንያህ፣ ዘባድያህ፣ አሳሄል፣ ሸሚራሞት፣ የሆናታን፣ አዶንያስ፣ ጦቢያህ እና ቶብአዶኒያህ ይገኙ ነበር፤ ካህናቱ ኤሊሻማ እና ኢዮራምም አብረዋቸው ነበሩ።+ 9 እነሱም በይሁዳ ማስተማር ጀመሩ፤ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍም ይዘው ነበር፤+ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር። ሚልክያስ 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን* ከአፉ ሊሹ ይገባል፤+ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው።
12 ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና* በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ።+
8 ከእነሱ ጋር ሌዋውያኑ ሸማያህ፣ ነታንያህ፣ ዘባድያህ፣ አሳሄል፣ ሸሚራሞት፣ የሆናታን፣ አዶንያስ፣ ጦቢያህ እና ቶብአዶኒያህ ይገኙ ነበር፤ ካህናቱ ኤሊሻማ እና ኢዮራምም አብረዋቸው ነበሩ።+ 9 እነሱም በይሁዳ ማስተማር ጀመሩ፤ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍም ይዘው ነበር፤+ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር።