14 በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤+ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15 አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ+ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤+ አንተም እጅግ ትደሰታለህ።+