-
ኢሳይያስ 42:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣
እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው?
በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም?
-
-
ኤርምያስ 40:2, 3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ኤርምያስን ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አምላክህ ይሖዋ በዚህ ስፍራ ላይ ይህ ጥፋት እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል፤ 3 በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁና ቃሉን ስላልታዘዛችሁ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ይህን ጥፋት አመጣ። ይህ ነገር በእናንተ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው።+
-