-
ዘፀአት 23:10, 11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “ለስድስት ዓመት መሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ አዝመራውንም ሰብስብ።+ 11 በሰባተኛው ዓመት ግን መሬትህን አትረሰው፤ እንዲሁ ተወው። በሕዝብህ መካከል ያሉ ድሆች ከዚያ ይበላሉ፤ ከእነሱ የተረፈውንም የዱር አራዊት ይበሉታል። በወይን እርሻህም ሆነ በወይራ ዛፍ እርሻህ እንደዚሁ ታደርጋለህ።
-
-
ዘሌዋውያን 25:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ የምታርፍበት ሰንበት ይኸውም የይሖዋ ሰንበት ይሁን። በእርሻህ ላይ ዘር አትዝራ ወይም ወይንህን አትግረዝ። 5 በማሳህ ላይ የበቀለውን ገቦ* አትጨድ፤ ያልተገረዘውን ወይንህን ፍሬ አትልቀም። ምድሪቱ ለአንድ ዓመት ሙሉ በሙሉ ማረፍ ይኖርባታል።
-