14 ስለዚህ እባክህ መኳንንታችን ለመላው ጉባኤ ተወካይ ሆነው ያገልግሉ፤+ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ በከተሞቻችን በሙሉ የሚገኙ ሰዎችም ከእያንዳንዱ ከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ጋር በተወሰነው ጊዜ ይምጡ፤ በዚህ ጉዳይ የተነሳ የመጣብን የአምላካችን የሚነድ ቁጣ እስኪመለስ ድረስ እንዲህ ብናደርግ የተሻለ ነው።”
15 ይሁን እንጂ የአሳሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያህዘያህ ይህን ሐሳብ ተቃወሙ፤ ሌዋውያኑ መሹላምና ሻበታይም+ ተባበሯቸው።